ምሳሌ 5:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ደግሞም እንዲህ ትላለህ፦ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው ወቀሳን ናቀ! 13 የአስተማሪዎቼን ቃል አላዳመጥኩም፤መምህሮቼንም በጥሞና አልሰማሁም። ዮሐንስ 3:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 መጥፎ ነገር የሚያደርግ* ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ እንዲሁም ሥራው እንዳይጋለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።