ዘፀአት 15:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚያም የአሮን እህት ነቢዪቱ ሚርያም አታሞ አነሳች፤ ሴቶቹም ሁሉ አታሞ እየመቱና እየጨፈሩ ተከተሏት። 21 ሚርያምም ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች እንዲህ ስትል ዘመረች፦ “በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ስላለ ለይሖዋ ዘምሩ።+ ፈረሱንና ፈረሰኛውን ባሕር ውስጥ ጣላቸው።”+ አስቴር 9:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከዋና ከተማዋ ውጭ በሚገኙ የገጠር ከተሞች የሚኖሩት አይሁዳውያን አዳር የተባለውን ወር 14ኛ ቀን የሐሴትና የግብዣ ቀን፣ የፈንጠዝያ ቀንና+ አንዳቸው ለሌላው ምግብ የሚልኩበት ጊዜ+ እንዲሆን ያደረጉት በዚህ የተነሳ ነው። አስቴር 9:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ምክንያቱም እነዚህ ቀናት አይሁዳውያኑ ከጠላቶቻቸው ያረፉባቸውና ሐዘናቸው ወደ ሐሴት፣ ለቅሷቸውም ወደ ፈንጠዝያ የተለወጠባቸው ቀናት ናቸው።+ እነዚህን ቀናት የግብዣና የደስታ እንዲሁም አንዳቸው ለሌላው ምግብ የሚልኩባቸውና ለድሆች ምጽዋት የሚሰጡባቸው ቀናት አድርገው እንዲያከብሩ ታዘው ነበር።
20 ከዚያም የአሮን እህት ነቢዪቱ ሚርያም አታሞ አነሳች፤ ሴቶቹም ሁሉ አታሞ እየመቱና እየጨፈሩ ተከተሏት። 21 ሚርያምም ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች እንዲህ ስትል ዘመረች፦ “በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ስላለ ለይሖዋ ዘምሩ።+ ፈረሱንና ፈረሰኛውን ባሕር ውስጥ ጣላቸው።”+
19 ከዋና ከተማዋ ውጭ በሚገኙ የገጠር ከተሞች የሚኖሩት አይሁዳውያን አዳር የተባለውን ወር 14ኛ ቀን የሐሴትና የግብዣ ቀን፣ የፈንጠዝያ ቀንና+ አንዳቸው ለሌላው ምግብ የሚልኩበት ጊዜ+ እንዲሆን ያደረጉት በዚህ የተነሳ ነው።
22 ምክንያቱም እነዚህ ቀናት አይሁዳውያኑ ከጠላቶቻቸው ያረፉባቸውና ሐዘናቸው ወደ ሐሴት፣ ለቅሷቸውም ወደ ፈንጠዝያ የተለወጠባቸው ቀናት ናቸው።+ እነዚህን ቀናት የግብዣና የደስታ እንዲሁም አንዳቸው ለሌላው ምግብ የሚልኩባቸውና ለድሆች ምጽዋት የሚሰጡባቸው ቀናት አድርገው እንዲያከብሩ ታዘው ነበር።