1 ሳሙኤል 14:41, 42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 ሳኦልም ይሖዋን “የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ በቱሚም+ አማካኝነት መልስ ስጠን!” አለው። ከዚያም ዮናታንና ሳኦል ተመረጡ፤ ሕዝቡም ነፃ ሆነ። 42 በዚህ ጊዜ ሳኦል “ከእኔና ከልጄ ከዮናታን ማን እንደሆነ ለመለየት ዕጣ ጣሉ”+ አለ። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወጣ። የሐዋርያት ሥራ 1:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከዚያም እንዲህ ብለው ጸለዩ፦ “የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቀው ይሖዋ* ሆይ፣+ ከእነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል የመረጥከውን አመልክተን፤ የሐዋርያት ሥራ 1:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ከዚያም በሁለቱ ሰዎች ላይ ዕጣ ጣሉ፤+ ዕጣውም ለማትያስ ወጣና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቆጠረ።*
41 ሳኦልም ይሖዋን “የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ በቱሚም+ አማካኝነት መልስ ስጠን!” አለው። ከዚያም ዮናታንና ሳኦል ተመረጡ፤ ሕዝቡም ነፃ ሆነ። 42 በዚህ ጊዜ ሳኦል “ከእኔና ከልጄ ከዮናታን ማን እንደሆነ ለመለየት ዕጣ ጣሉ”+ አለ። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወጣ።