መዝሙር 18:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+ አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።+ መዝሙር 91:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣* እታደገዋለሁ።+ ስሜን ስለሚያውቅ* እጠብቀዋለሁ።+