ዘዳግም 8:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+ ዘዳግም 8:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እንዲሁም ወደፊት መልካም እንዲሆንልህ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን ሲል+ አባቶችህ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መግቦሃል።+ ምሳሌ 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ተግሣጽን ያዛት፤ አትልቀቃትም።+ ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።+ ዕብራውያን 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ተግሣጽ የምትቀበሉበት* አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ መከራ ሲደርስባችሁ መጽናት ያስፈልጋችኋል። አምላክ የያዛችሁ እንደ ልጆቹ አድርጎ ነው።+ ለመሆኑ አባቱ የማይገሥጸው ልጅ ማን ነው?+ ዕብራውያን 12:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ተግሣጽ ለጊዜው የሚያስደስት አይመስልም፤ ይልቁንም ያስከፋል፤* በኋላ ግን በተግሣጽ ሥልጠና ላገኙ ሰዎች የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ ያፈራላቸዋል።
7 ተግሣጽ የምትቀበሉበት* አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ መከራ ሲደርስባችሁ መጽናት ያስፈልጋችኋል። አምላክ የያዛችሁ እንደ ልጆቹ አድርጎ ነው።+ ለመሆኑ አባቱ የማይገሥጸው ልጅ ማን ነው?+
11 እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ተግሣጽ ለጊዜው የሚያስደስት አይመስልም፤ ይልቁንም ያስከፋል፤* በኋላ ግን በተግሣጽ ሥልጠና ላገኙ ሰዎች የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ ያፈራላቸዋል።