-
1 ነገሥት 2:22-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ሰለሞን ለእናቱ እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ለአዶንያስ ሹነማዊቷን አቢሻግን ብቻ ለምን ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ+ ስለሆነ ንግሥናም ጠይቂለት እንጂ፤+ ካህኑ አብያታርና የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብም+ እየደገፉት ነው።”
23 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን እንዲህ ሲል በይሖዋ ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በመጠየቁ ሕይወቱን ሳያጣ ቢቀር* አምላክ ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣብኝ። 24 አሁንም በሚገባ ባጸናኝ፣+ በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ ባስቀመጠኝና በገባው ቃል መሠረት ቤት በሠራልኝ*+ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አዶንያስ በዛሬዋ ዕለት ይገደላል።”+
-