ኢዮብ 31:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ጠላቴ በደረሰበት ጥፋት ደስ ብሎኝ ያውቃል?+ወይስ ክፉ ነገር ስለደረሰበት ሐሴት አድርጌ አውቃለሁ? ምሳሌ 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤+በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም።+ ምሳሌ 25:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ጠላትህ* ቢራብ ምግብ ስጠው፤ቢጠማ ውኃ ስጠው፤+22 ይህን ብታደርግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፤*+ይሖዋም ወሮታ ይከፍልሃል።