9 ከዚያም ሌላ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ሌላም ሕልም አለምኩ። አሁን ደግሞ ፀሐይ፣ ጨረቃና 11 ከዋክብት ሲሰግዱልኝ አየሁ።”+ 10 ሕልሙንም ለአባቱና ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ አባቱም ገሠጸው፤ እንዲህም አለው፦ “ይህ ያለምከው ሕልም ፍቺ ምንድን ነው? እኔም ሆንኩ እናትህና ወንድሞችህ መጥተን መሬት ላይ ተደፍተን እንድንሰግድልህ ታስባለህ?” 11 ወንድሞቹም ይበልጥ ቀኑበት፤+ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።