-
ዘኁልቁ 25:6-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ሆኖም ልክ በዚህ ጊዜ አንድ እስራኤላዊ፣ ሙሴና በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እያለቀሰ ያለው የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት+ ይዞ ወደ ወንድሞቹ መጣ። 7 የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ ይህን ሲመለከት ከማኅበረሰቡ መሃል ወዲያው ብድግ ብሎ ጦር አነሳ። 8 ከዚያም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ በመግባት ሁለቱንም ወጋቸው፤ እስራኤላዊውን ወጋው፤ እሷንም ሆዷ* ላይ ወጋት። በዚህ ጊዜ መቅሰፍቱ ከእስራኤል ልጆች ላይ ተወገደ።+
-