-
1 ነገሥት 21:8-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ስለሆነም በአክዓብ ስም ደብዳቤዎች ጽፋ በእሱ ማኅተም አተመቻቸው፤+ ደብዳቤዎቹንም ናቡቴ በሚኖርበት ከተማ ወደሚገኙት ሽማግሌዎችና+ ታላላቅ ሰዎች ላከቻቸው። 9 በደብዳቤዎቹም ላይ እንዲህ ስትል ጻፈች፦ “ጾም አውጁ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት በክብር ቦታ ላይ አስቀምጡት። 10 ሁለት የማይረቡ ሰዎችንም አምጥታችሁ ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና ‘አምላክንና ንጉሡን ተራግመሃል!’+ በማለት እንዲመሠክሩበት አድርጉ።+ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።”+
11 በመሆኑም የከተማዋ ሰዎች ማለትም እሱ በሚኖርበት ከተማ ያሉት ሽማግሌዎችና ታላላቅ ሰዎች ኤልዛቤል በላከችላቸው ደብዳቤዎች ላይ በተጻፈው መሠረት አደረጉ።
-