-
ዘዳግም 17:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል።+ ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም።
-
-
1 ነገሥት 11:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ይሁንና ንጉሥ ሰለሞን ከፈርዖን ልጅ+ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን+ ማለትም ሞዓባውያን፣+ አሞናውያን፣+ ኤዶማውያን፣ ሲዶናውያንና+ ሂታውያን+ ሴቶችን አፈቀረ። 2 እነሱም ይሖዋ ለእስራኤላውያን “ከእነሱ ጋር አትቀላቀሉ፤* እነሱም ከእናንተ ጋር አይቀላቀሉ፤ አለዚያ ያለምንም ጥርጥር ልባችሁ አማልክታቸውን ወደ መከተል እንዲያዘነብል ያደርጉታል”+ ብሎ ከነገራቸው ብሔራት ወገን ነበሩ። ሆኖም ሰለሞን ከእነሱ ጋር ተጣበቀ፤ ደግሞም አፈቀራቸው። 3 እሱም ልዕልቶች የሆኑ 700 ሚስቶች እንዲሁም 300 ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ቀስ በቀስ ልቡ ወደ ሌላ እንዲያዘነብል አደረጉት።*
-