መዝሙር 104:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እንዲሁም የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፣+ፊትን የሚያበራ ዘይትናየሰውን ልብ የሚያበረታ እህል እንዲገኝ ነው።+ ማቴዎስ 27:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ሐሞት* የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤+ እሱ ግን ከቀመሰው በኋላ ሊጠጣው አልፈለገም።