ሩት 3:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ይባርክሽ። ሀብታምም ሆኑ ድሃ፣ ወጣት ወንዶችን ተከትለሽ ባለመሄድሽ ከበፊቱ ይልቅ+ አሁን ያሳየሽው ታማኝ ፍቅር በለጠ። 11 ስለዚህ የእኔ ልጅ፣ አትፍሪ። አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽን የከተማው* ሰው ሁሉ ስለሚያውቅ ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ።+ ምሳሌ 12:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ጥሩ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት፤+አሳፋሪ* ሚስት ግን አጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።+ ምሳሌ 19:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ቤትና ሀብት ከአባቶች ይወረሳል፤ልባም ሚስት ግን የምትገኘው ከይሖዋ ነው።+
10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ይባርክሽ። ሀብታምም ሆኑ ድሃ፣ ወጣት ወንዶችን ተከትለሽ ባለመሄድሽ ከበፊቱ ይልቅ+ አሁን ያሳየሽው ታማኝ ፍቅር በለጠ። 11 ስለዚህ የእኔ ልጅ፣ አትፍሪ። አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽን የከተማው* ሰው ሁሉ ስለሚያውቅ ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ።+