1 ሳሙኤል 25:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ስለሆነም አቢጋኤል+ ወዲያውኑ 200 ዳቦ፣ ሁለት እንስራ የወይን ጠጅ፣ ታርደው የተሰናዱ አምስት በጎች፣ አምስት የሲህ መስፈሪያ* ቆሎ፣ 100 የዘቢብ ቂጣ እንዲሁም 200 የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳ ሁሉንም በአህዮች ላይ ጫነች።+ ምሳሌ 19:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ 1 ጢሞቴዎስ 2:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ለአምላክ ያደርን ነን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉት እንደሚገባ በመልካም ሥራ ይዋቡ።+ ዕብራውያን 13:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤+ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና።+
18 ስለሆነም አቢጋኤል+ ወዲያውኑ 200 ዳቦ፣ ሁለት እንስራ የወይን ጠጅ፣ ታርደው የተሰናዱ አምስት በጎች፣ አምስት የሲህ መስፈሪያ* ቆሎ፣ 100 የዘቢብ ቂጣ እንዲሁም 200 የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳ ሁሉንም በአህዮች ላይ ጫነች።+