መክብብ 5:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 እኔ ያየሁት መልካምና ተገቢ የሆነ ነገር፣ ሰው እውነተኛው አምላክ በሰጠው አጭር የሕይወት ዘመን ሁሉ መብላቱና መጠጣቱ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በደከመበትና በትጋት ባከናወነው ሥራ ሁሉ ደስታ ማግኘቱ ነው፤+ ይህ ብድራቱ* ነውና።+ 19 ደግሞም እውነተኛው አምላክ ለሰው ሀብትና ቁሳዊ ንብረት+ ብሎም በእነዚህ ነገሮች የመደሰት ችሎታ ሲሰጠው ብድራቱን* ተቀብሎ በትጋት በሚያከናውነው ሥራ መደሰት ይገባዋል። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።+ ኢሳይያስ 65:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤+ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።+ 22 እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም። የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፤+የመረጥኳቸው አገልጋዮቼም በእጃቸው ሥራ የተሟላ እርካታ ያገኛሉ።
18 እኔ ያየሁት መልካምና ተገቢ የሆነ ነገር፣ ሰው እውነተኛው አምላክ በሰጠው አጭር የሕይወት ዘመን ሁሉ መብላቱና መጠጣቱ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በደከመበትና በትጋት ባከናወነው ሥራ ሁሉ ደስታ ማግኘቱ ነው፤+ ይህ ብድራቱ* ነውና።+ 19 ደግሞም እውነተኛው አምላክ ለሰው ሀብትና ቁሳዊ ንብረት+ ብሎም በእነዚህ ነገሮች የመደሰት ችሎታ ሲሰጠው ብድራቱን* ተቀብሎ በትጋት በሚያከናውነው ሥራ መደሰት ይገባዋል። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።+
21 ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤+ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።+ 22 እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም። የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፤+የመረጥኳቸው አገልጋዮቼም በእጃቸው ሥራ የተሟላ እርካታ ያገኛሉ።