1 ሳሙኤል 17:46 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 ዛሬ ይሖዋ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጥሃል፤+ እኔም አንተን ገድዬ ራስህን እቆርጠዋለሁ፤ በዚህ ቀን የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎችም በእስራኤል አምላክ እንዳለ ያውቃሉ።+ መዝሙር 102:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ብሔራት የይሖዋን ስም፣የምድር ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።+ 16 ይሖዋ ጽዮንን ዳግመኛ ይገነባልና፤+በክብሩም ይገለጣል።+ ኢሳይያስ 37:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ ከእጁ አድነን።”+
46 ዛሬ ይሖዋ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጥሃል፤+ እኔም አንተን ገድዬ ራስህን እቆርጠዋለሁ፤ በዚህ ቀን የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎችም በእስራኤል አምላክ እንዳለ ያውቃሉ።+