ዘፀአት 17:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ምረጥና የአባይን ወንዝ የመታህበትን በትር+ ይዘህ ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ። በትሩን በእጅህ ይዘህ ሂድ። 6 እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገኘው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።”+ ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ። ዘኁልቁ 20:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ሙሴም ይህን ካለ በኋላ እጁን አንስቶ ዓለቱን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ውኃውም ይንዶለዶል ጀመር፤ ማኅበረሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።+
5 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ምረጥና የአባይን ወንዝ የመታህበትን በትር+ ይዘህ ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ። በትሩን በእጅህ ይዘህ ሂድ። 6 እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገኘው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።”+ ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ።