ማርቆስ 15:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ከእሱም ጋር ሁለት ዘራፊዎችን፣ አንዱን በቀኙ ሌላውን ደግሞ በግራው በእንጨት ላይ ሰቀሉ።+ ሉቃስ 22:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 ይህን የምላችሁ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ’+ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ መፈጸም ስላለበት ነው። ስለ እኔ የተነገረው ነገር ፍጻሜውን እያገኘ ነውና።”+ ሉቃስ 23:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ወንጀለኞች የሆኑ ሌሎች ሁለት ሰዎችም ከእሱ ጋር ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር።+ 33 የራስ ቅል+ ወደተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስን በዚያ ከወንጀለኞቹ ጋር በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ወንጀለኞቹም አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው ተሰቅለው ነበር።+
32 ወንጀለኞች የሆኑ ሌሎች ሁለት ሰዎችም ከእሱ ጋር ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር።+ 33 የራስ ቅል+ ወደተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስን በዚያ ከወንጀለኞቹ ጋር በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ወንጀለኞቹም አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው ተሰቅለው ነበር።+