ኢሳይያስ 1:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ስለዚህ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣የእስራኤል ኃያል አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እንግዲያው ስሙ! ባላጋራዎቼን አጠፋለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል፤የሚነድ ቁጣውንም አፍስሷል።+ በጽዮን መሠረቶቿን የሚበላ እሳት አንድዷል።+ ሕዝቅኤል 5:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ።+ በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣+ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ።
13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ።+ በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣+ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ።