21 አንቺም በልብሽ እንዲህ ትያለሽ፦
‘እኔ ልጆቼን በሞት ያጣሁና መሃን
እንዲሁም በምርኮ የተወሰድኩና እስረኛ የሆንኩ ሴት ሆኜ ሳለ
እነዚህን ልጆች የወለደልኝ ማን ነው?
ያሳደጋቸውስ ማን ነው?+
እነሆ፣ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤+
ታዲያ እነዚህ ከየት መጡ?’”+
22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ እጄን ለብሔራት አነሳለሁ፤
ምልክቴንም ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ።+
ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው ይዘው ያመጧቸዋል፤
ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሟቸዋል።+