መሳፍንት 6:36, 37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ከዚያም ጌድዮን እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን የምታድን ከሆነ+ 37 ይኸው አውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ፀጉር አስቀምጣለሁ። በዙሪያው ያለው ምድር በሙሉ ደረቅ ሆኖ የበግ ፀጉሩ ላይ ብቻ ጤዛ ከተገኘ ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን እንደምታድን አውቃለሁ።” ኢሳይያስ 37:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 “‘ይህም ምልክት ይሆንሃል፦* በዚህ ዓመት የገቦውን እህል* ትበላላችሁ፤ በሁለተኛውም ዓመት ከዚያው ላይ የበቀለውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ዘር ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁም፤ እንዲሁም ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።+ ኢሳይያስ 38:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ የተናገረውን ቃል እንደሚፈጽም የሚያሳየው ይሖዋ የሰጠህ ምልክት ይህ ነው፦+ 8 በአካዝ ደረጃ* ላይ ወደ ታች የወረደውን የፀሐይ ጥላ ወደ ኋላ አሥር ደረጃ እንዲመለስ አደርገዋለሁ።”’”+ በመሆኑም ወደ ታች ወርዶ የነበረው የፀሐይ ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
36 ከዚያም ጌድዮን እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን የምታድን ከሆነ+ 37 ይኸው አውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ፀጉር አስቀምጣለሁ። በዙሪያው ያለው ምድር በሙሉ ደረቅ ሆኖ የበግ ፀጉሩ ላይ ብቻ ጤዛ ከተገኘ ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን እንደምታድን አውቃለሁ።”
30 “‘ይህም ምልክት ይሆንሃል፦* በዚህ ዓመት የገቦውን እህል* ትበላላችሁ፤ በሁለተኛውም ዓመት ከዚያው ላይ የበቀለውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ዘር ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁም፤ እንዲሁም ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።+
7 ይሖዋ የተናገረውን ቃል እንደሚፈጽም የሚያሳየው ይሖዋ የሰጠህ ምልክት ይህ ነው፦+ 8 በአካዝ ደረጃ* ላይ ወደ ታች የወረደውን የፀሐይ ጥላ ወደ ኋላ አሥር ደረጃ እንዲመለስ አደርገዋለሁ።”’”+ በመሆኑም ወደ ታች ወርዶ የነበረው የፀሐይ ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።