የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢያሱ 10:8-14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ከዚያም ይሖዋ ኢያሱን “በእጅህ አሳልፌ ስለሰጠኋቸው+ አትፍራቸው።+ አንዳቸውም እንኳ ሊቋቋሙህ አይችሉም”+ አለው። 9 ኢያሱም ከጊልጋል በመነሳት ሌሊቱን ሙሉ ሲገሰግስ አድሮ ድንገት መጣባቸው። 10 ይሖዋም በእስራኤላውያን ፊት ግራ እንዲጋቡ አደረጋቸው፤+ እነሱም ገባኦን ላይ ክፉኛ ጨፈጨፏቸው፤ ወደ ቤትሆሮን አቀበት በሚወስደው መንገድ ላይ በማሳደድ እስከ አዜቃ እና እስከ መቄዳ ድረስ መቷቸው። 11 እነሱም ከእስራኤላውያን በመሸሽ የቤትሆሮንን ቁልቁለት እየወረዱ ሳሉ እስከ አዜቃ ድረስ ይሖዋ ከሰማይ ትላልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ እነሱም ሞቱ። እንዲያውም በእስራኤላውያን ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት ይበልጣሉ።

      12 ይሖዋ አሞራውያንን ከእስራኤላውያን ፊት ባባረረበት ዕለት ኢያሱ በእስራኤላውያን ፊት ይሖዋን እንዲህ አለው፦

      “ፀሐይ ሆይ፣ በገባኦን ላይ ቁሚ፤+

      አንቺም ጨረቃ ሆይ፣ በአይሎን ሸለቆ* ላይ ቀጥ በይ!”

      13 በመሆኑም ብሔሩ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህስ በያሻር መጽሐፍ+ ላይ ተጽፎ የሚገኝ አይደለም? ፀሐይ በሰማይ መካከል ባለችበት ቆመች፤ ለአንድ ቀን ያህል ለመጥለቅ አልቸኮለችም። 14 ይሖዋ የሰውን ቃል የሰማበት+ እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ ፈጽሞ አልነበረም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ለእስራኤል እየተዋጋ ነበር።+

  • 2 ሳሙኤል 5:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም መጥቶ በዚያ መታቸው። እሱም “ይሖዋ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በፊቴ ደረማመሳቸው” አለ።+ ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም*+ ብሎ ጠራው።

  • 1 ዜና መዋዕል 14:10-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ዳዊትም “ወጥቼ ፍልስጤማውያንን ልግጠም? በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ?” ሲል አምላክን ጠየቀ። ይሖዋም “አዎ ውጣ፤ እኔም በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” አለው።+ 11 በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም+ ወጥቶ በዚያ መታቸው። ከዚያም ዳዊት “እውነተኛው አምላክ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በእጄ ደረማመሳቸው” አለ። ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም* ብለው ጠሩት። 12 ፍልስጤማውያንም አማልክታቸውን በዚያ ጥለው ሸሹ፤ ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረትም በእሳት አቃጠሏቸው።+

      13 ከጊዜ በኋላ ፍልስጤማውያን ሸለቆውን* እንደገና ወረሩ።+ 14 ዳዊት ዳግመኛ አምላክን ጠየቀ፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ እንዲህ አለው፦ “እነሱን ለመግጠም በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዙርና በባካ* ቁጥቋጦዎቹ ፊት መጥተህ ግጠማቸው።+ 15 ደግሞም በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ጥቃት ሰንዝር፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።”+ 16 ስለዚህ ዳዊት ልክ እውነተኛው አምላክ እንዳዘዘው አደረገ፤+ የፍልስጤማውያንንም ሠራዊት ከገባኦን አንስቶ እስከ ጌዜር+ ድረስ መቷቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ