7 “ብቻ አንተ ደፋርና ብርቱ ሁን፤ አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። በምትሄድበት በየትኛውም ቦታ ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን እንድትችል+ ከዚህ ሕግ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ 8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤+ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤+ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።+