11 “የምድር ነጋዴዎችም ከዚህ በኋላ ብዛት ያለውን ሸቀጣቸውን የሚገዛቸው ስለማይኖር ስለ እሷ ያለቅሳሉ እንዲሁም ያዝናሉ፤ 12 ብዛት ያለው ሸቀጣቸውም ወርቅን፣ ብርን፣ የከበሩ ድንጋዮችን፣ ዕንቁን፣ ጥሩ በፍታን፣ ሐምራዊ ጨርቅን፣ ሐርንና ደማቅ ቀይ ጨርቅን ያካተተ ነው፤ በተጨማሪም ጥሩ መዓዛ ካለው እንጨት የተሠራ ነገር ሁሉ፣ ከዝሆን ጥርስ፣ ውድ ከሆነ እንጨት፣ ከመዳብ፣ ከብረትና ከእብነ በረድ የተሠራ ማንኛውም ዓይነት ዕቃ ሁሉ ይገኝበታል፤