ኢሳይያስ 13:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣*+የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣+አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።+ ኢሳይያስ 13:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 የሚያላዝኑ ፍጥረታት በማማዎቿ፣ቀበሮዎችም በሚያማምሩ ቤተ መንግሥቶቿ ውስጥ ሆነው ይጮኻሉ። ጊዜዋ ቀርቧል፤ ቀኖቿም አይራዘሙም።”+