ዘፀአት 32:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ‘ዘራችሁን በሰማያት ላይ እንዳሉት ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ለዘላለም ርስት አድርጎ እንዲወርሰውም ለዘራችሁ ለመስጠት ያሰብኩትን ይህን ምድር በሙሉ እሰጠዋለሁ’+ በማለት በራስህ የማልክላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስታውስ።” ዘሌዋውያን 26:41, 42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 እኔም እነሱን ወደ ጠላቶቻቸው ምድር በማምጣት+ እቃወማቸዋለሁ።+ “‘ምናልባትም ያልተገረዘው* ልባቸው በዚያ ጊዜ ትሑት ይሆናል፤+ የስህተታቸውንም ዋጋ ይከፍላሉ። 42 እኔም ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳንና ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤+ እንዲሁም ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤+ ምድሪቱንም አስባለሁ። መዝሙር 106:43-45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤+እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤+ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።+ 44 እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።+ 45 ለእነሱ ሲል ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ታላቅ በሆነው* ታማኝ ፍቅሩ ተገፋፍቶ ያዝንላቸው* ነበር።+
13 ‘ዘራችሁን በሰማያት ላይ እንዳሉት ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ለዘላለም ርስት አድርጎ እንዲወርሰውም ለዘራችሁ ለመስጠት ያሰብኩትን ይህን ምድር በሙሉ እሰጠዋለሁ’+ በማለት በራስህ የማልክላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስታውስ።”
41 እኔም እነሱን ወደ ጠላቶቻቸው ምድር በማምጣት+ እቃወማቸዋለሁ።+ “‘ምናልባትም ያልተገረዘው* ልባቸው በዚያ ጊዜ ትሑት ይሆናል፤+ የስህተታቸውንም ዋጋ ይከፍላሉ። 42 እኔም ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳንና ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤+ እንዲሁም ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤+ ምድሪቱንም አስባለሁ።
43 ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤+እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤+ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።+ 44 እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።+ 45 ለእነሱ ሲል ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ታላቅ በሆነው* ታማኝ ፍቅሩ ተገፋፍቶ ያዝንላቸው* ነበር።+