ዘፀአት 20:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+ ዘሌዋውያን 23:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “‘ለስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት+ ይኸውም ቅዱስ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ይህ የይሖዋ ሰንበት ነው።+
9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+
3 “‘ለስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት+ ይኸውም ቅዱስ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ይህ የይሖዋ ሰንበት ነው።+