የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 18:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 “‘ከልጆችህ መካከል የትኛውንም ለሞሎክ እንዲሰጥ* አታድርግ።+ በዚህ መንገድ የአምላክህን ስም አታርክስ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

  • 2 ዜና መዋዕል 28:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 አካዝ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 20 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አላደረገም።+

  • 2 ዜና መዋዕል 28:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 በተጨማሪም በሂኖም ልጅ ሸለቆ* የሚጨስ መሥዋዕት ያቀረበ ከመሆኑም ሌላ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሙ የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል+ ወንዶች ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 33:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ 55 ዓመት ገዛ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 33:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 በሂኖም ልጅ ሸለቆም+ የገዛ ልጆቹን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤+ አስማተኛ፣+ ሟርተኛና መተተኛ ሆነ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ።+ ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ።

  • ኢሳይያስ 57:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 በትላልቅ ዛፎች መካከል፣

      ቅጠሉ በተንዠረገገም ዛፍ ሥር ሁሉ በስሜት የተቃጠላችሁ፣+

      በሸለቆዎች* ውስጥ፣ በቋጥኞች መካከል

      ልጆችን የምታርዱ አይደላችሁም?+

  • ኤርምያስ 7:31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 ያላዘዝኩትንና በልቤ እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል+ በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ የሚገኘውን የቶፌትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል።’+

  • ኤርምያስ 32:35
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 35 በተጨማሪም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት አሳልፈው ለመስጠት በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ ያሉትን የባአልን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል፤+ ይሁዳን ኃጢአት ለማሠራት ይህን አስጸያፊ ነገር እንዲፈጽሙ እኔ አላዘዝኩም፤+ ፈጽሞም በልቤ አላሰብኩም።’*

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ