ኤርምያስ 39:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከለዳውያንም የንጉሡን ቤትና* የሕዝቡን ቤቶች አቃጠሉ፤+ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ።+ ሚክያስ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።+