ኢሳይያስ 13:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ+ በራእይ ያየው በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ ኢሳይያስ 13:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣*+የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣+አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።+ ኢሳይያስ 14:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ ብለህ ትተርታለህ፦* “ሌሎችን አስገድዶ ሲያሠራ የነበረው* እንዴት አበቃለት! ጭቆናውስ እንዴት አከተመ!+ ኢሳይያስ 14:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “የጃርት መኖሪያና ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋት መጥረጊያም እጠርጋታለሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።