2 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንና በእውነተኛው አምላክ ቤት ውስጥ ካሉት ዕቃዎች መካከል የተወሰኑትን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤+ እሱም በሰናኦር+ ምድር ወደሚገኘው ወደ አምላኩ ቤት አመጣቸው። ዕቃዎቹን በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አስቀመጣቸው።+
3 ከዚያም ንጉሡ የቤተ መንግሥቱ ዋና ባለሥልጣን የሆነውን አሽፈኔዝን ከንጉሡና ከመሳፍንቱ ዘር የሆኑትን ጨምሮ አንዳንድ እስራኤላውያንን እንዲያመጣ አዘዘው።+