መዝሙር 16:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ ድርሻዬ፣ ዕጣ ፋንታዬና+ ጽዋዬ+ ነው። ርስቴን ትጠብቅልኛለህ። መዝሙር 73:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ሰውነቴም ሆነ ልቤ ሊዝል ይችላል፤አምላክ ግን ለዘላለም የልቤ ዓለትና ድርሻዬ ነው።+ መዝሙር 142:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ። ደግሞም “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤+በሕያዋን ምድር ያለኸኝ አንተ ብቻ* ነህ” እላለሁ።