የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 28:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+

  • ዘዳግም 28:36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 ይሖዋ አንተንና በላይህ ያነገሥከውን ንጉሥ፣ አንተም ሆንክ አባቶችህ ወደማታውቁት ብሔር ይወስዳችኋል፤+ እዚያም ሌሎች አማልክትን ይኸውም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትን ታገለግላለህ።+

  • 2 ነገሥት 24:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።

  • 2 ነገሥት 25:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዷቸው፤ ከዚያም ናቡከደነጾር የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤ በመዳብ የእግር ብረት አስሮም ወደ ባቢሎን ወሰደው።+

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 በይሖዋ የተቀባው፣+ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ ጥልቅ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ፤+

      “በእሱ ጥላ ሥር በብሔራት መካከል እንኖራለን” ብለን ነበር።

  • ሕዝቅኤል 12:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 መረቤን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል።+ ከዚያም ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ምድሪቱን ግን አያይም፤ በዚያም ይሞታል።+

  • ዳንኤል 1:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ከዚያም ንጉሡ የቤተ መንግሥቱ ዋና ባለሥልጣን የሆነውን አሽፈኔዝን ከንጉሡና ከመሳፍንቱ ዘር የሆኑትን ጨምሮ አንዳንድ እስራኤላውያንን* እንዲያመጣ አዘዘው።+

  • ዳንኤል 1:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ከእነሱ መካከል ከይሁዳ ነገድ የሆኑት ዳንኤል፣*+ ሃናንያህ፣* ሚሳኤልና* አዛርያስ* ይገኙበታል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ