6 ይሖዋ ሰይፍ አለው፤ ሰይፉም በደም ትሸፈናለች።
በስብ፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች ደም
እንዲሁም በአውራ በጎች ኩላሊት ስብ ትለወሳለች።
ይሖዋ በቦስራ መሥዋዕት፣
በኤዶምም ምድር
ታላቅ እርድ ያዘጋጃልና።+
7 የዱር በሬዎች ከእነሱ ጋር ይወድቃሉ፤
ወይፈኖችም ከብርቱ ኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ።
ምድራቸውም በደም ይሸፈናል፤
አፈራቸውም በስብ ይርሳል።”
8 ይሖዋ የሚበቀልበት ቀን፣+
በጽዮን ላይ ለተፈጸመው በደል ቅጣት የሚያስፈጽምበት ዓመት አለውና።+