2 ነገሥት 21:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል።+ 2 ነገሥት 24:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይህ ነገር ይሖዋ ባዘዘው መሠረት በይሁዳ ላይ የደረሰው ይሁዳን ከፊቱ ለማጥፋት ነው፤+ ይህም የሆነው ምናሴ በሠራቸው ኃጢአቶች ሁሉ የተነሳ ነው፤+ 4 ንጹሕ ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ ነው፤+ ይሖዋም ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም።+ ኤርምያስ 2:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች* ደም ቆሽሸዋል፤+ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።+ ሕዝቅኤል 9:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ በጣም ታላቅ ነው።+ ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤+ ከተማዋም በክፋት ተሞልታለች።+ ‘ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል፤ ይሖዋም አያይም’ ይላሉና።+
16 ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል።+
3 ይህ ነገር ይሖዋ ባዘዘው መሠረት በይሁዳ ላይ የደረሰው ይሁዳን ከፊቱ ለማጥፋት ነው፤+ ይህም የሆነው ምናሴ በሠራቸው ኃጢአቶች ሁሉ የተነሳ ነው፤+ 4 ንጹሕ ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ ነው፤+ ይሖዋም ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም።+
9 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ በጣም ታላቅ ነው።+ ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤+ ከተማዋም በክፋት ተሞልታለች።+ ‘ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል፤ ይሖዋም አያይም’ ይላሉና።+