15 ኪሩቦቹም ወደ ላይ ተነሱ፤ በኬባር ወንዝ+ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት እነዚሁ ነበሩ፤ 16 ኪሩቦቹ ሲንቀሳቀሱ፣ መንኮራኩሮቹም አጠገባቸው ሆነው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ኪሩቦቹ ከምድር በላይ ከፍ ከፍ ለማለት ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ሲዘረጉ መንኮራኩሮቹ ከአጠገባቸው አይለዩም ወይም አይርቁም ነበር።+ 17 እነሱ ሲቆሙ፣ መንኮራኩሮቹም ይቆማሉ፤ እነሱ ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በውስጣቸው ነበርና።