1 ነገሥት 22:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ+ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው+ አየሁ። መዝሙር 99:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 99 ይሖዋ ነገሠ።+ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ። እሱ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን ተቀምጧል።+ ምድር ትናወጥ። ኢሳይያስ 6:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ንጉሥ ዖዝያ በሞተበት ዓመት+ ይሖዋን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤+ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ራእይ 4:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ከዚያም ወዲያውኑ የአምላክ መንፈስ ወረደብኝ፦ እነሆም፣ በሰማይ አንድ ዙፋን ተቀምጦ ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበር።+
19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ+ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው+ አየሁ።