ኤርምያስ 14:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ።+ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም።+ የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።+ ኤርምያስ 28:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩ ሃናንያህን+ እንዲህ አለው፦ “ሃናንያህ ሆይ፣ እባክህ ስማ! ይሖዋ ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።+ 16 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ። በይሖዋ ላይ ዓመፅ ስላነሳሳህ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’”+ ኤርምያስ 29:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ሟርተኞች አያታሏችሁ፤+ የሚያልሙትንም ሕልም አትስሙ። 9 ‘በስሜ የሚተነብዩላችሁ ሐሰት ነውና። እኔ አልላክኋቸውም’+ ይላል ይሖዋ።”’”
14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ።+ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም።+ የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።+
15 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩ ሃናንያህን+ እንዲህ አለው፦ “ሃናንያህ ሆይ፣ እባክህ ስማ! ይሖዋ ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።+ 16 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ። በይሖዋ ላይ ዓመፅ ስላነሳሳህ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’”+
8 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ሟርተኞች አያታሏችሁ፤+ የሚያልሙትንም ሕልም አትስሙ። 9 ‘በስሜ የሚተነብዩላችሁ ሐሰት ነውና። እኔ አልላክኋቸውም’+ ይላል ይሖዋ።”’”