-
ዘኁልቁ 14:13-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ሙሴ ግን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንዲህ ካደረግክ ይህን ሕዝብ በኃይልህ ከመካከላቸው ስታወጣ ያዩ ግብፃውያን መስማታቸው አይቀርም፤+ 14 እነሱ ደግሞ የሰሙትን ነገር ለዚህ ምድር ነዋሪዎች ይናገራሉ። እነሱም ቢሆኑ አንተ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ መካከል እንዳለህና+ ፊት ለፊት+ እንደተገለጥክላቸው ሰምተዋል። አንተ ይሖዋ ነህ፤ ደመናህም በላያቸው ላይ ቆሟል፤ ቀን ቀን በደመና ዓምድ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ከፊት ከፊታቸው ትሄዳለህ።+ 15 እንግዲህ ይህን ሕዝብ በሙሉ በአንዴ ብትፈጀው* የአንተን ዝና የሰሙ ብሔራት እንዲህ ማለታቸው አይቀርም፦ 16 ‘ይሖዋ ይህን ሕዝብ፣ ሊሰጠው ወደማለለት ምድር ሊያስገባው ስላልቻለ በምድረ በዳ ፈጀው።’+
-