-
ዘፀአት 22:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 “ከሕዝቤ መካከል አብሮህ ላለ ችግረኛ ገንዘብ ብታበድር እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁንበት። ወለድም አትጠይቁት።+
-
-
ዘሌዋውያን 6:4, 5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ሆኖ ቢገኝ የሰረቀውን፣ ቀምቶ ወይም አጭበርብሮ የወሰደውን አሊያም በአደራ ተሰጥቶት የነበረውን ወይም ደግሞ ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፤ 5 አሊያም በሐሰት የማለበትን ማንኛውንም ነገር ይመልስ፤ ሙሉ ካሳ ይክፈል፤+ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበት። በደለኛ መሆኑ በተረጋገጠበትም ዕለት ለባለቤቱ ይሰጠዋል።
-