-
ኤርምያስ 3:6-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 በንጉሥ ኢዮስያስ+ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።+ 7 ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤+ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።+ 8 ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ+ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት።+ ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።+
-