12 ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር ይሞታል ወይም በመካከልሽ በረሃብ ያልቃል። ሌላ አንድ ሦስተኛ ደግሞ በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል።+ የመጨረሻውን አንድ ሦስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው እበትነዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ 13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ።+ በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣+ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ።