ምሳሌ 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅ+ማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።+ ሕዝቅኤል 33:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “‘እንዲሁም ክፉውን ሰው “በእርግጥ ትሞታለህ” ባልኩት ጊዜ ከኃጢአቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣+ 15 ደግሞም ክፉው ሰው መያዣ አድርጎ የወሰደውን ቢመልስ፣+ የሰረቀውን መልሶ ቢሰጥና+ መጥፎ ነገር ከመፈጸም ተቆጥቦ ሕይወት የሚያስገኙትን ደንቦች ቢከተል፣ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።+ ፈጽሞ አይሞትም። ያዕቆብ 5:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ወንድሞቼ፣ ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ከእውነት መንገድ ስቶ ቢወጣና ሌላ ሰው ቢመልሰው፣ 20 ኃጢአተኛን ከስህተት ጎዳናው የሚመልስ ማንኛውም ሰው+ ኃጢአተኛውን* ከሞት እንደሚያድንና ብዙ ኃጢአትን እንደሚሸፍን እወቁ።+
14 “‘እንዲሁም ክፉውን ሰው “በእርግጥ ትሞታለህ” ባልኩት ጊዜ ከኃጢአቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣+ 15 ደግሞም ክፉው ሰው መያዣ አድርጎ የወሰደውን ቢመልስ፣+ የሰረቀውን መልሶ ቢሰጥና+ መጥፎ ነገር ከመፈጸም ተቆጥቦ ሕይወት የሚያስገኙትን ደንቦች ቢከተል፣ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።+ ፈጽሞ አይሞትም።
19 ወንድሞቼ፣ ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ከእውነት መንገድ ስቶ ቢወጣና ሌላ ሰው ቢመልሰው፣ 20 ኃጢአተኛን ከስህተት ጎዳናው የሚመልስ ማንኛውም ሰው+ ኃጢአተኛውን* ከሞት እንደሚያድንና ብዙ ኃጢአትን እንደሚሸፍን እወቁ።+