ኢሳይያስ 6:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ሱራፌልም ከእሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፎች ነበሯቸው። እያንዳንዱ* በሁለቱ ክንፍ ፊቱን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ እግሩን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ ደግሞ ይበር ነበር። ሕዝቅኤል 10:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እነዚህ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው፤+ በመሆኑም ኪሩቦች መሆናቸውን አወቅኩ። 21 አራቱም፣ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው፤ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰው እጆች የሚመስሉ ነገሮች ነበሯቸው።+ ራእይ 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እነዚህ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ ክንፎቹ በዙሪያቸውና በውስጥ በኩል በዓይኖች የተሞሉ ናቸው።+ ያለማቋረጥም ቀንና ሌሊት “የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፣+ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ* አምላክ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”+ ይላሉ።
2 ሱራፌልም ከእሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፎች ነበሯቸው። እያንዳንዱ* በሁለቱ ክንፍ ፊቱን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ እግሩን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ ደግሞ ይበር ነበር።
20 እነዚህ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው፤+ በመሆኑም ኪሩቦች መሆናቸውን አወቅኩ። 21 አራቱም፣ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው፤ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰው እጆች የሚመስሉ ነገሮች ነበሯቸው።+
8 እነዚህ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ ክንፎቹ በዙሪያቸውና በውስጥ በኩል በዓይኖች የተሞሉ ናቸው።+ ያለማቋረጥም ቀንና ሌሊት “የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፣+ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ* አምላክ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”+ ይላሉ።