-
ዳንኤል 4:13-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 “‘በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ራእዮቹን ስመለከት ቅዱስ የሆነ አንድ ጠባቂ ከሰማያት ሲወርድ አየሁ።+ 14 እሱም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ዛፉን ቁረጡ፤+ ቅርንጫፎቹን ጨፍጭፉ፤ ቅጠሎቹን አራግፉ፤ ፍሬውንም በትኑ! የዱር እንስሳቱ ከሥሩ፣ ወፎቹም ከቅርንጫፎቹ ላይ ይሽሹ። 15 ጉቶው ግን በብረትና በመዳብ ታስሮ በሜዳ ሣር መካከል ከነሥሩ መሬት ውስጥ ይቆይ። በሰማያትም ጠል ይረስርስ፤ ዕጣ ፋንታውም በምድር ተክሎች መካከል ከአራዊት ጋር ይሁን።+ 16 ልቡ ከሰው ልብ ይለወጥ፤ የአውሬም ልብ ይሰጠው፤ ሰባት ዘመናትም+ ይለፉበት።+
-