ዳንኤል 5:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ቤልሻዛር የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው አባቱ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የወርቅና የብር ዕቃዎች፣+ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጧቸው አዘዘ። 3 በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም፣ በአምላክ ቤት ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዷቸውን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ጠጡባቸው።
2 ቤልሻዛር የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው አባቱ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የወርቅና የብር ዕቃዎች፣+ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጧቸው አዘዘ። 3 በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም፣ በአምላክ ቤት ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዷቸውን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ጠጡባቸው።