ዳንኤል 8:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “በዘመነ መንግሥታቸውም መገባደጃ ላይ በደለኞቹ እስከ መጨረሻ* በደል ሲፈጽሙ፣ ግራ የሚያጋቡ አባባሎችን የሚረዳ* አስፈሪ መልክ ያለው ንጉሥ ይነሳል። 24 ኃይሉ እጅግ ታላቅ ይሆናል፤ በገዛ ኃይሉ ግን አይደለም። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጥፋት* ያደርሳል፤ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለታል። በኃያላን ሰዎችና በቅዱሳኑ ሕዝብ ላይ ጥፋት ያደርሳል።+ ዳንኤል 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ከወንዙ ውኃ በላይ ያለውና በፍታ የለበሰው ሰው መልስ ሲሰጥ ሰማሁ። እሱም ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማያት ዘርግቶ ለዘላለም ሕያው በሆነው+ በመማል እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “ከተወሰነ ዘመን፣ ዘመናትና የዘመን እኩሌታ* በኋላ ነው። የቅዱሱ ሕዝብ ኃይል ተደምስሶ እንዳበቃ+ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ።” ራእይ 13:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ቅዱሳኑን እንዲዋጋና ድል እንዲያደርጋቸው ተፈቀደለት፤+ ደግሞም በነገድ፣ በሕዝብ፣ በቋንቋና በብሔር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
23 “በዘመነ መንግሥታቸውም መገባደጃ ላይ በደለኞቹ እስከ መጨረሻ* በደል ሲፈጽሙ፣ ግራ የሚያጋቡ አባባሎችን የሚረዳ* አስፈሪ መልክ ያለው ንጉሥ ይነሳል። 24 ኃይሉ እጅግ ታላቅ ይሆናል፤ በገዛ ኃይሉ ግን አይደለም። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጥፋት* ያደርሳል፤ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለታል። በኃያላን ሰዎችና በቅዱሳኑ ሕዝብ ላይ ጥፋት ያደርሳል።+
7 ከዚያም ከወንዙ ውኃ በላይ ያለውና በፍታ የለበሰው ሰው መልስ ሲሰጥ ሰማሁ። እሱም ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማያት ዘርግቶ ለዘላለም ሕያው በሆነው+ በመማል እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “ከተወሰነ ዘመን፣ ዘመናትና የዘመን እኩሌታ* በኋላ ነው። የቅዱሱ ሕዝብ ኃይል ተደምስሶ እንዳበቃ+ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ።”