-
ዕዝራ 9:6, 7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 እንዲህም አልኩ፦ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፣ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ማድረግ አሳፈረኝ፤ አሸማቀቀኝ፤ ምክንያቱም አምላኬ ሆይ፣ የፈጸምናቸው ስህተቶች በአናታችን ላይ ተቆልለዋል፤ በደላችንም ከመብዛቱ የተነሳ እስከ ሰማይ ደርሷል።+ 7 ከአባቶቻችን ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የፈጸምነው በደል ታላቅ ነው፤+ በሠራናቸውም ስህተቶች የተነሳ ይኸው ዛሬ እንደሚታየው እኛም ሆንን ነገሥታታችንና ካህናታችን በሌሎች አገሮች ነገሥታት እጅ ወድቀን ለሰይፍ፣+ ለምርኮ፣+ ለብዝበዛና+ ለውርደት ተዳርገናል።+
-
-
ነህምያ 9:33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
33 በእኛ ላይ በደረሰው ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ምክንያቱም አንተ ማንኛውንም ነገር ያደረግከው በታማኝነት ነው፤ ክፉ ነገር የፈጸምነው እኛ ነን።+
-