19 ምክንያቱም እኛ ማለትም እኔ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ+ የሰበክንላችሁ የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “አዎ” ሆኖ እያለ “አይደለም” ሊሆን አይችልም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ጋር በተያያዘ “አዎ” የተባለው “አዎ” ሆኗል። 20 አምላክ የሰጣቸው ተስፋዎች የቱንም ያህል ብዙ ቢሆኑም በእሱ አማካኝነት “አዎ” ሆነዋል።+ ስለዚህ እኛ ለአምላክ ክብር እንድንሰጥ በእሱ አማካኝነት ለአምላክ “አሜን” እንላለን።+