መዝሙር 48:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣+በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።+ ዳንኤል 8:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከእነሱ መካከል ከአንደኛው፣ አንድ ሌላ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና* ውብ ወደሆነችው ምድር*+ በጣም እያደገ ሄደ። ዳንኤል 11:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በእሱ ላይ የሚመጣው እንደፈለገው ያደርጋል፤ በፊቱም የሚቆም አይኖርም። ውብ በሆነችው* ምድር+ ላይ ይቆማል፤ የማጥፋትም ኃይል ይኖረዋል። ዳንኤል 11:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 ንጉሣዊ* ድንኳኖቹንም በታላቁ ባሕርና ቅዱስ በሆነው ውብ* ተራራ+ መካከል ይተክላል፤ እሱም ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ የሚረዳውም አይኖርም።